Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ኢትዮጵያ የምታስተናግደዉ 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባዔ ሀገራችን ያሳካቻቸው ተጨባጭ ልምዶችን የምታካፍልበት መድረክ ነው

ኢትዮጵያ የምታስተናግደዉ 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባዔ ሀገራችን ያሳካቻቸው ተጨባጭ ልምዶችን የምታካፍልበት መድረክ ነው

September 8, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

2ኛዉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን ጉባኤ የምታስተናግደዉ ለተሳታፊዎች ተጨባጭ ልምዶችን በማካፈል ጭምር ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እየሠራች ትገኛለች፡፡

መላዉ ኢትዮጵያውያን በተከታታይ ዓመት በሚያደርጉት የላቀ ተሳትፎ የራሳቸዉን ክብረ ወሰን እያሻሻሉ በአንድ ጀምበር ከ700 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል ችለዋል፡፡ ይህም ለዓለም ትምህርት መኾን የሚችል ተነሣሽነትና ቁርጠኝነት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ነባር ከተሞችን በማዘመን የውኃ ብክለትን ለመቆጣጠር በሰፊዉ እየሠራች ነው፡፡ የአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻ ልማትን ብቻ ብንወስድ ከእንጦጦ ከፍተኛ ቦታዎች የሚነሡ የአዋሽ ተፋሰስ ገባር ወንዞችን በተሳካ ኹኔታ እያከመች ነው፤ ይህም አጠቃላይ የአዋሽ ወንዝን የማከም አካል ተደርጎ የሚወሰድ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡

ወንዞቻችን ንጹሕ፣ ማራኪና ለመናፈሻነት የሚመረጡ እንዲኾኑ በትኩረት መሥራታችን ለሌሎች አገራት በትልቁ አስተማሪ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን በልዩ ትኩረት በማምረትና በመጠቀምም አብነት መኾን የምትችል ሀገር ናት፡፡ ከተሞቿ እና ኢንዱስትሪዎቿ በስፋት የሚጠቀሙት ኃይል ከውኃ፣ ከነፋስ እና ከፀሐይ ኃይል የሚመነጭ ነው፡፡

ከራሷ አልፋ ሌሎች የቀጣናዉን ሀገራት የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ በማድረግም ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ጉልህ ሚና የምትጫወት ሀገር ናት፡፡

ኢትዮጵያ የምታመነጫውን ታድሽ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በማጋራት በኤልትሪክ ኃይል መሰረተ ልማትም ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በቀጣናው ሀገራት መካከል ትስስርና ቅንጅት እየፈጠረች ነው፡፡ እንደ ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ እና ታንዛንያ ያሉ አገራት ከኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ከኾኑ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን በስፋት በመጠቀሟ ለማገዶ ሲባል የሚጨፈጨፍ ደንን በእጅጉ ቀንሳለች፡፡ የበካይ ጋዝ ምንጭ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን መጠን ለመቀነስ እና በሂደትም በታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች ለመተካት በስፋት እየሠራች ነው፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ከ100 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ መንግሥት በልዩ ልዩ ማበረታቻዎች ኹሉም የተሽከርካሪ ባለቤቶች ወደ ታዳሽ ኃይል ተጠቃሚነት እንዲገቡ እየሠራ ነው፤ ይህም በጉባኤዉ ተሳታፊዎች ልምድ እንደሚወሰድበት ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤን ስታስተናግድ ጉባኤዉ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ ሐሳቦች የሚንሸራሸሩበት፣ አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽኦዋ እምንት ኾኖ በጉዳቱ ክፉኛ እየተጎዳች መኾኑ ታውቆ የማካካሻ እና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድበት እንዱኾን አበክራ ትሠራለች፡፡

መረጃው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: #addisabebaEthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ኮናቴ ወደ ማድሪድ?

Next Post

አልቫሬዝ ታገደ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
አልቫሬዝ ታገደ

አልቫሬዝ ታገደ

ሊቨርኩሰን አሰልጣኝ ሾመ

ሊቨርኩሰን አሰልጣኝ ሾመ

በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የተጣለው እገዳ

በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የተጣለው እገዳ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?