እንግሊዛዊው የመሃል ተከላካይ ሰኞ ምሽት ወደ ሊቨርፑል ለመዘዋወር የህክምና ሂደት ላይ እንዳለ በፓላሱ አሰልጣኝ ጣልቃ ገብነት ዝውውሩ ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል።
ጌሂ የዝውውር መስኮቱ ሊዘጋ ሰዓታት በቀሩበት ሰዓት በመርሲሳይዱ ክለብ ይገኝ የነበረ ሲሆን፤ ዝውውሩ መጨናገፉን ተከትሎ ወደ ለንደኑ ክለብ ተመልሷል። ፓላስ ተጫዋቹ ለመሸጥ ተጋዶ የነበረበት ምክንያት ውሉ ሊያበቃ መቃረቡን ተከትሎ የነበረ ቢሆንም፤ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር የቡድን ስብስባቸው መሳሳቱን ተከትሎ ተጫዋቹን መልሰውታል።
ክሪስታል ፓላስ አሁን ላይ ተጫዋቹን ለተጨማሪ አመታት በክለቡ እንዲቆይ የሚያስችለውን የተሻሻ ጥቅማጥቅም የተካተተበት ኮንትራት ቢያቀርብለትም ማርክ ጌሂ ውድቅ ማድረጉ ተዘግቧል። በክለቡ ውሳኔ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ነው የተባለው ጌሂ ውሉን አጠናቆ የመልቀቅ ውሳኔ ላይ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












