የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአሜሪካ ወታደሮች ከቬንዙዌላ ትሬን ዲ ኣራጓ ቡድን የአደንዛዥ ዕፅ እያዘዋወረች ነው ባሏት ትንሽዬ መርከብ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ነው የተናገሩት።
በማህበራዊ ትስስር ገፃቸውም መርከቧ ስትነድ የሚያሳይ ምስል በማጋራት ፤ ማንም ወደ አሜሪካ አደንዛዥ ዕፅ ለማስገባት ያቀደ አካል ሊያስብበት ይገባል የሚል መልዕክታቸውን አያይዘዋል።
አክለውም በጥቃቱ 11 ሰዎች ቢሞቱም የአሜሪካ አንድም ወታደር ስላለመጎዳቱ አስታውቀዋል። የትራምፕን መግለጫ ተከትሎ በቬኔዙዌላና አሜሪካ መካከል ያለው ቅራኔ እንደሚባባስ ይጠበቃል፤
ዶናልድ ትራምፕ የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ቡድኖችን በስፉት ይደግፉሉ በሚል ክስ ማቅረብ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፤ ማክሰኞ ጠዋት የተፈፀመው ይህ ጥቃት የትራምፕ አስተዳደር በካሪቢያን ወታደራዊ ይዞታውን ማስፉፉት ከጀመረበት የባለፈው ወር ወዲህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












