ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ፣ ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ላይ እያሴሩ ነው ሲሉ ወቀሱ።
ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት በቻይና ግዙፉ ቲያናንመን አደባባይ ለምዕራቡ ዓለም አስፈሪ ነው የተባለውን ወታደራዊ ትዕይንት ቤይጂንግ ማድረጓን ተከትሎ ነው።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ “ከጦርነት እና ሰላም ዓለም ትምረጥ “የሚል ሀሳብ መስጠታቸውም ትርጓሜውን የስጋት አድርጎባቸዋል።
ጃፓን በሁለተኛው ዓለም ጦርነት እጅ የሰጠችበትን 80ኛ ዓመት የድል በዓል ላይ ቤይጂንግ የሞስኮውን ፑቲንን ፣የቴህራኑን ፔዜሽኪያንን እና የፒዮንግያንጉን ኪም ጆንግ ኡንን ማስተናገዷ መድረኩን ዓለም አቀፋዊ እንዲሆን በር ከፍቶለታል።
በርካታ አሜሪካውያን ለቻይናውያን ድል ህይወታቸውን ገብረዋል ያሉት ትራምፕ ቤይጂንግ፣ ሞስኮና ፒዮንግያንግ በዋሽንግተን ላይ እያሴሩ ይገኛል በሚል ከሰዋል።
ለፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እንኳን ደስ አሎት የሚል መልዕክት ቢያስተላልፉም ትራምፕ እያሴራችሁችብንም ቢሆን ለኪምና ፑቲንም ይድረስልኝ በሚል ”ንዴትም ፣እኛንም ታሳቢ አድርጉ እንጂ” የሚል ሀሳብ ያዘለ መልዕክት ልከዋል።
ዘገባው የዋሽንግተን ፖስት ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












