እሁድ እኩለ ሌሊት የኩናር እና ናንጋርሃርን ምስራቃዊ ግዛቶች ባናወጠው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ600 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል ።
በምስራቅ አፍጋኒስታን በሬክተር ስኬል 6 ሆኖ በተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 622 ሰዎች ሲሞቱ ከ1500 በላይ መጎዳታቸውን በአፍጋኒስታን የታሊባን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል ።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከጃላላባድ ከተማ በስተሰሜን-ምስራቅ 27 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የተከሰተ ሲሆን መንቀጥቀጡ እስከ አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና እስላማባድ ድረስ ተሰምቷል።
በአከባቢው በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እና የጎርፍ አደጋ በተፈጠረው የመሬት መንሸራተት ተከትሎ የነብስ አድን ስራውን አዳጋች እንዳደረገው ተነግሯል ። አሁንም በህይወት የተረፉ ሰዎችን የማፈላለግ ስራ ተጠናከሮ መቀጠሉ ተመላክቷል።
ዘገባው የቢቢሲ እና ዘ ጋርዲያን ነው
በ -ሰላማዊት ወልደገሪማ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












