ሊቨርፑል አሌክሳንደር ኢሳቅን ከኒውካስትል ዩናይትድ ለማስፈረም ከስምምነት ደረሰ።
የመርሲሳይዱ ክለብ ትውልደ ኤርትራዊውን አጥቂ ከኒውካስትል ለማስፈረም የተስማማው የእንግሊዝ የተጫዋቾች ክብረወሰንን በማሻሻል መሆኑን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ሊቨርፑል ለተጫዋቹ ግዢ በጥቅል 130 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ የሚያደርግ ሲሆን፣በ2023 ቼልሲ ኤንዞ ፈርናንዴዝን ካስፈረመበት 106 ሚሊዮን ፓውንድ በኋላ አዲሱ ክብረወሰን በመሆን ተመዝግቧል።
የ25 አመቱ ኢሳቅ ዛሬ ሌሊት የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የህክምና ሂዳቱን አጠናቆ እስከ 2031 የሚያቆየውን የ6 አመት ውል ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።
ኒውካስትል ዩናይትድ ቀደም ብሎ ተጫዋቹን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ፣ኢሳቅ በክለቡ ላይ በማመጽ በልምምድ ስፍራ እና በሁለት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ሳይሰለፍ መቅረቱ ይታወሳል።
ማግፓይሶቹ ከቀናት በፊት ተተኪውን አጥቂ ኒክ ቮልትማደን በማስፈረሙ የኢሳቅን ዝውውር ያፋጥናል የሚለው መዘገቡም አይዘነጋም። ሊቨርፑል የኢሳቅን ዝውውር ሲያጠናቅቅ በክረምት ለተጫዋቾች ግዢ ያወጣውን ወጪ ወደ ግማሽ ቢሊዮን ፓውንድ ያስጠጋዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












