ሩሲያ ለሊቱን በዩክሬን ዋና ከተማ ኬቭ በፈፀመችው ከፍተኛ የድሮን ጥቃት 15 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል። በጥቃቱ በተከሰተው ከፍተኛ ፍንዳታ ሳቢያ እስከማለዳው ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች እሳትና ጭስ መስተዋሉንም የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ሩሲያ ኬይቭ ለሊቱን የተፈፀመችው ይህ የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካን አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር በአላስካ ከተወያዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
የኬቭ ከተማ ወታደራዊ አስተዳደር እንደተናገሩት በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል አራቱ ህጻናት ስለመሆናቸው ተናግረዋል። አስተዳደሩ አክለውም በጥቃቱ በዳርኒስኪ ከተማ ከአምስት በላይ የመኖሪያ ህንጻዎች ስለመውደማቸውም ገልጸዋል።
በዋና ከተማዋ ኬቭ እንዲሁ በርካታ ህንጻዎች መውደማቸውንና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከፍርስራሽ ውስጥ ሰዎችን ለማውጣት ርብርብ እያረጉ መሆኑን ገልጸዋል። የኬቭ ከንቲባ በበኩላቸው ጥቃቱን ተለከትሎ ባንዲራ ዝቅ ተደርጎ እንደሚውለበለብና፤ ህዝባዊ ዝግጅቶች መሰረዛቸውን ተናግረዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸቸው ፑቲን ከመወያያ ጠረፔዛ ይልቅ ሚሳኤልን መርጠዋል ሲሉ ወቅሰዋቸዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












