ታላቅ የሰብዓዊ መብት ንግግር – ማርቲን ሉተር ኪንግ “I Have a Dream”
ልክ በዛሬው ቀን እ.ኤ.አ በ1963 ነሐሴ 28 የአሜሪካ የቤተ ክርስቲያን መሪ እና የሰብዓዊ መብት ተሞጋች ማርቲን ሉተር ኪንግ ታዋቂ የሆነውን “I Have a Dream” የሚለውን ንግግር በዋሽንግተን በተካሄደው “March on Washington for Jobs and Freedom” በተባለው ታላቅ የሰብዓዊ መብት ሰልፍ ላይ ተናገረ።
በዚያ ጊዜ ከ200,000 በላይ ሰዎች በሊንከን መታሰቢያ ቦታ ላይ ተሰብስበው የእኩልነት መብትና የዘር ግፍ እንዲቆም ጠይቀው ነበር፡፡
ማርቲን በንግግሩ ውስጥ በፍትህ፣ በሰላምና በእኩል እድል ላይ የተመሠረተ አሜሪካ እንድትገነባ በአጽንኦት የተናገረ ሲሆን ብዙዎችም ይህንን ንግግር እንደ 20ኛው ክፍለ ዘመን ተፅዕኖ ፈጣሪ የፖለቲካ እና የሰብዓዊ መብት ንግግር ይቆጥራሉ።
“I Have a Dream” እስከ ዛሬ ድረስ የፍትህ፣ የእኩልነት መብት እና የሰላም ንድፈ ሀሳብ እንደሆነ ይታሰባል፤ በዓለም ሁሉ ያሉ የሰብዓዊ መብት እንቅስቃሴዎችን ለመፍጠር ኃይል ሆኖ አሁንም እያገለገለ ይገኛል፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን












