የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁን “የጦር ጀግና” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።
“እሱ ጥሩ ሰው ነው፤ እሱ እየተዋጋ ነው፤ እሱ የጦርነት ጀግና ነው” በማለት ትራምፕ ኔታንያሁን አሞካሽተዋል። አያይዘውም “እኔም ጀግና እንደሆንኩ እገምታለሁ” በማለት ገልጸዋል፡፡
ትራምፕ፣ የእስራኤሉን ፕሬዝዳንት ተጠያቂ ለማድረግ የተደረገውን ጥረት ውድቅ በማድረግ “እስር ቤት ሊጥሉት እየሞከሩ ነው” ብለዋል። ቀደም ሲል ከሃማስ ጋር ባደረገው ድርድር የእስራኤል ታጋቾችን ለማስፈታት “ጠንክሮ ሰርቷል” ሲሉም አሞግሰዋቸዋል፡፡
ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












