ኢራን “ታላቋን እስራኤል” የመገንባት ውጥን ለዓለም እና ለቀጠናው ሰላም ስጋት ነው ስትል አሳሰበች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ዓላማ ዓለምን ስጋት ውስጥ የማስገባት ነው በሚል መግለጫ ሰጥተዋል። 34 ሙስሊም እና ዓረብ አገራት እንዲሁም ድርጅቶች እስራኤል የመስፋፋት ውጥኑን መቀልበስ አለባት በሚልም አውግዘዋል።
ጋዛውያንን በሀይል ማፈናቀል እንዲሁም የታላቋ እስራኤል ምስረታ ሂደት የምድርን ሰላም ያውካል ብላለች ኢራን። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ሙስሊም አገራት የእስራኤል ድርጊት አግባብነት የሌለው መሆኑን መረዳት እንዳለበትም መግለጫው ይተነትናል።
የጽ’ዮናውያኑ ጥቃት በኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይወገዛል ይላል የእነ አያቶላህ አሊ ኻምኒ መግለጫ። እስራኤል በጋዛ ላይ ጦርነት ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ ከ61 ሺህ በላይ ሰዎች ከፍልስጤማውያን በኩል ህይወታቸውን አጥተዋል።
ሲ ኤን ኤን እንዳስነበበው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












