Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ከ65ሺህ በላይ ታጣቂዎችን በተሃድሶ ሂደት አልፈዋል ተባለ

ከ65ሺህ በላይ ታጣቂዎችን በተሃድሶ ሂደት አልፈዋል ተባለ

August 13, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን 65ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሃድሶ ሂደት በማሳለፍ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ገለጸ።

የፌዴራል መንግሥት የቀድሞ ታጣቂዎችን ለማሰልጠን፤ ለስልጠና ማዕከላት ጥገና፣ ለምግብ፣ ለአልባሳት እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች እስከአሁን አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ማውጣቱ ተጠቁሟል።

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸውን ጉዳዮች በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ኮሚሽኑ 65ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎች በተሐድሶ ሂደት አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ገልጸዋል።

እነዚህ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመጡት ትጥቅ የማስረከብ፣ የማረጋገጥ፣ ምዝገባ የማካሄድ፣ የተሀድሶና የስነ ልቦና ሥልጠና በመውሰድ እንዲሁም የዲጂታል መታወቂያ አግኝተው ወደ ህብረተሰቡ የተቀላቀሉ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንደተናገሩት፤ ኮሚሽኑ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ሰላማዊና ምርታማ ህይወት ለማሸጋገር በርካታ ስራዎችን አከናውኗል።

ኮሚሽኑ በሰላም ስምምነት እንዲሁም በመንግስት፣ በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች የቀረቡ ጥሪዎችን ተቀብለው ወደ ሰላም የሚመጡ የቀድሞ ታጣቂዎች የሀገሪቱ የሰላምና የልማት ኃይል እንዲሆኑ ለማስቻል እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ወዲህ ከ65ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሃድሶ ሂደት በማሳለፍ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉን ጠቁመዋል። ይህም በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች መሆኑንም አስታውቀዋል።

የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተስፋለም ይህደጎ በተለያዩ ክልሎች የተሐድሶ ማዕከላትን በማቋቋም የቀድሞ ታጣቂዎችን በዘላቂነት እንዲቋቋሙ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በትግራይ ክልል በሶስት ማዕከላት የቀድሞ ታጣቂዎችን ተቀብሎ በተሐድሶ ሂደት በማሳለፍ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የፌዴራል መንግሥት ለስልጠና ማዕከላት ጥገና፣ ለምግብ፣ ለአልባሳት እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ማውጣቱን ጠቁመው፤ የቀድሞ ታጣቂዎቹን ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ ለእያንዳንዳቸው 90ሺህ 400 ብር መሰጠቱን እና በአጠቃላይ ከአጋር አካላት አምስት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

በየትኛውም አካባቢ ያሉ ታጣቂዎች የሕዝብንና የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው የተሐድሶ መርሐ ግብሩ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል። የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያ በመግለጫቸው፤ ኮሚሽኑ ወደ ስራ ከገባ ወዲህ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲቀላቀሉ መደረጉን ተናግረዋል።

የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግና ፈታኝ ተግባር መሆኑንና የመንግስት፣ የህዝብንና የአጋር አካላትን ትብብር እንደሚጠይቅ አመልክተው፤ ይህ የሚመራበት የመልሶ ማቋቋሚያ ሰነድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ሰነዱ በሚመለከታቸው አካላት የተተቸና በቅርቡ እንደሚጸድቅ ጠቁመው፤ በሰነዱ መሰረት የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ወደ ማቋቋም ተግባር እንደሚገባ ገልጸዋል። በዚህም በተሐድሶ ሂደት አልፈው የኮሚሽኑን ህጋዊ መታወቂያ የያዙ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ቀደመ ስራቸው እንደሚመለሱና ጥቅማ ጥቅሞች እንደሚከበርላቸውም ጨምረው አስታውቀዋል።

በተሃድሶ ሂደት አልፈው ከህብረተሰቡ ጋር ለተቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

የተመድ ማስጠንቀቂያ ለሩሲያና እስራኤል

Next Post

የትራምፕና ዘለንስኪ ውይይት

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የትራምፕና ዘለንስኪ ውይይት

የትራምፕና ዘለንስኪ ውይይት

ፓልሜራስ የኖቲንግሃም ፎረስቱን ግብ ጠባቂ ካልሎስ ሚጌልን ለማስፈረም ድርድር ጀመረ

ፓልሜራስ የኖቲንግሃም ፎረስቱን ግብ ጠባቂ ካልሎስ ሚጌልን ለማስፈረም ድርድር ጀመረ

ፍቅረኛዋን የደበደበችው አትሌት ይቅርታ ጠየቀች

ፍቅረኛዋን የደበደበችው አትሌት ይቅርታ ጠየቀች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?