በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል ያለው ጦርነት ያበቃ ዘንድ ዜሌንስኪ ከፑቲን ጋር በአካል መነጋገር እፈልጋለሁ ማለታቸው ነው የተሰማው።
ዜሌንስኪ ቁጣዎች ተረጋግተው መነጋገር አለብን ሲሉም ተደምጠዋል። ከትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ያደረጉት ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ከፑቲን ጋር በቅርቡ እንደምንወያይ እጠብቃለሁ ሲሉም ተናግረዋል።
ዜሌንስኪ አክለውም ከጀርመኑ መራሔ መንግስት ፍሬዴሪክ ሜርዝ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን እና ከጣልያን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መወያየት እንደሚፈልጉም ገልጸዋል። የአውሮፓ ሀገራትም ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ውይይት ሊሳተፉ ይገባል ሲሉም ዜሌንስኪ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት 1260 ቀናትን እንዳስቆጠረ ፍራንስ 24 ዘግቧል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












