በ1992 የተመሰረተው ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር 25 አመታትን አስቆጥሯል።
የተመሰረተበትን 25ኛ አመት አስመልክቶ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን በነዚህ አመታት ውስጥ ከ1ሺህ 5መቶ በላይ አረጋውያን ድጋፍ መስጠቱንና ከ1ሺህ 5መቶ የሚልቁ ወጣቶችና ሴቶችን በማቋቋም ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ ተገልጿል።
ከ10 ሺህ 5መቶ በላይ ለሚሆኑ ወላጅ አጥ ህፃናትና ወጣቶች የትምህርትና የህክምና ሙሉ ወጪ በመሸፈን ከማስተማር በተጨማሪ ለቤተሰቦቻቸው የአስቤዛ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ነው በመግለጫው የተመላከተው።
ከ25 አመታት በፊት በአስር ብር መዋጮ ወደ ስራ የገባው ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር አሁን ላይ የሚሰጠውን የደግነት አገልግሎት በማስፋት በርካታ አቅመ ደካማ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ነው የተገለፀው።
በጋዜጣዊ መግለጫው መልዕክት ያስተላለፉት ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ባለፉት 25 አመታት ዜጎችን በምንም መስፈርት ሳይለይ ሲያገለግል የቆየ ተቋም መሆኑን አንስተዋል።
25ኛ አመት የምስረታ በዓሉን የደግነት ዘመናትን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ መሰናዶዎች ለተከታታይ ወራት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
2ኛው የቢላል አዋርድ መስከረም ወር ላይ እንደሚካሄድም ነው የተመላከተው።
በ-አክረም ኑርያ












