የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍን በክሬምሊን ቤተመንግስት ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል። ዊትኮፍ ሞስኮ የገቡት፣ ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ ላይ የማዕቀብ ዛቻ ባስተላለፉበት ወቅት መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን “አሰቃቂ ጦርነት” ለማስቆም ርምጃ ካልወሰደች ከባድ ማዕቀብ እንደሚጠብቃት እንዲሁም ከሞስኮ ጋር በሚገበያዩት ሀገራት ላይ በድጋሜ ማዕቀብ ሊጣልባቸው ይችላል ማለታቸው ይታወሳል።
ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ በኢስታንቡል የተደረገው ዩክሬን እና ሩሲያ ውይይት ጦርነቱን ወደ መጨረሻው ለማምጣት አልቻለም። የሞስኮ ወታደራዊ እና የፖለቲካ ቅድመ ሁኔታዎች ለኪዬቭ እና ለምዕራባውያን አጋሮቻቸው ተቀባይነት አለማግኘቱም ይታወቃል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












