ውሃ ሰማያዊዎቹ በጥር የዝውውር መስኮት ያስፈረሙትን ብራዚላዊ ተከላካይ ለላሊጋው ክለብ እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በውሰት መስጠታቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ማንችስተር ሲቲ እና ጂሮና በአንድ ባለቤት ስር የሚተዳደሩ ሲሆን፣ ባለፉት አመታት ሲቲ በርካታ ተጫዋቾችን በውሰት ለዚሁ ክለብ ሲሰጥ እንደነበር ይታወሳል። ቪክቶር ሬየስ በጥር የዝውውር መስኮት ከብራዚሉ ክለብ ፓልሜራስ ሲቲን በ35 ሚሊዮን ዩሮ ከተቀላቀለ ወዲህ 4 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ችሏል።
በክለቦች የአለም ዋንጫም ከዋይዳድ ካዛብላንካ ጋር በተደረገ ጨዋታ 90 ደቂቃ መጫወት ችሏል። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የ19 አመቱ ተጫዋች እንዲጎለብት ወደ ስፔን ላሊጋ ሸኝተውታል።
ሲቲ ከዚህ አስቀድሞ ሌላኛውን ብራዚላዊ የክንፍ ተጫዋቹን ሳቪኒሆ ለጂሮና በውሰት በመስጠት እንዲጎለብት ም፣ማድረጉ ይታወሳል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












