የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ24 ሰዓታት ውስጥ “ከፍተኛ” ያሉትን ታሪፍ በህንድ ላይ እንደሚጥሉ አስታወቁ።
የደልሂ ፖለቲከኞች ከሩሲያ የነዳጅ ምርት መግዛታቸው ያባሳጫቸው ትራምፕ፣ ህንድ ታማኝ የንግድ አጋር አልሆነችልንም በሚልም ወቅሰዋል። ህንድ ኢኮኖሚዋን ለመታደግ እና ብሄራዊ ጥቅምን ታሳቢ በማድረግ ከሞስኮ አሁንም ነዳጅ ማስገባት መቀጠል እንደምትችል ሊታወቅልኝ ይገባል ብላለች።
አውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ አመክንዮ የሌለው ክስ አቅርበውብኛል በሚልም ኒው ደልሂ ትከራከራለች። “ባለከፍተኛ ታሪፍ አገር ” በሚል ትራምፕ ህንድን ሲጠሩ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ25 በመቶው በተጨማሪ ከፍተኛ የተባለ ታሪፍ ሊጥሉባት እንደሆነ ይጠቁማል።
“ብዙ ቢዝነስ ከእኛ ጋር ይሰራሉ። ነገር ግን አንፈልጋቸውም።” በሚልም እንዲሁ አጣጥለዋል ትራምፕ። የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት የሞስኮን የጦር መሳሪያ ካዝና እየሞላ ነው ሲሉም የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን መንግስት ወቅሰዋል።
በ2024-25 የበጀት ዓመት የህንድና አሜሪካ የንግድ ልውውጥ $131.8 ቢሊዬን ሲደርስ ኒው ደልሂ $41.18 ቢሊዬን የንግድ ትርፍ አግኝታለች። ዋሽንግተን ደግሞ የንግድ ጉድለት ገጥሟት እንደነበር አይዘነጋም።
አር ቲ እንደዘገበው።
በ-ቢኒያም ካሴ












