ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር ከጳጉሜ 3 እስከ 5 2017 ዓ.ም በምታስታናግደውን ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በቂ ዝግጅት እያደረገች መሆኑ ተገለፀ።
ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ያላቸውን ተሰሚነት ከፍ የሚያደርግ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጻል።
አፍሪካውን በአየር ንብረት ለውጥ ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ሲሆን ከተረጅነት በመውጣት የመፍትሔው አካልም እንደሆኑ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳየት በእጅጉ የሚረዳ መሆኑ ነው የተገለጸው።
አፍሪካ ዝቅተኛ ጋዝ ልቅት ቢኖራትም ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ማምለጥ ባለመቻሏ አማራጭ መፍትሄ ላይ ለመምክር ያግዛል ብለዋል የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን።
በፓሪሱ ስምምነት ለአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቅት የሚለቁ ያደጉ አገራት ለታዳጊ አገራት የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ቢቀመጡ አተገባበሩ ዝቅተኛ መሆኑ ይቀመጣል። ይህ ጉባኤም አዲስና ጠተጨማሪ የአየር ንብረት ፋይናንስን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የሚፈረሙ አለም አቀፍ ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ አፍሪካውያን አቋማቸውን የሚያንጸባሩቁበት እንደሆነ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ከማስተናገድ ባሻገር የአረንጓዴ ልማት ስኬታማ ተሞክሮዋን እንደምታቀርብ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በግብርና ፣በትራንስፖርት እና በኢነርጂ ዘርፎች ከብክለት ነጻ ለማድረግ እያለናወነቻቸው ያሉ ስራዎች የምታሳይበት መድረክ ይሆናልም ተብሎ ይጠበቃል ።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












