የደንብ ማስከበር ተግባራቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት ላይ የድብደባ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ ስራውን እያጣራ መሆኑን የን/lፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ጀሞ መስታወት ፋብሪካ አካባቢ ነው።
ተከሳሾች ዮሀንስ ከበደ፣ ሠዒድ ሠይፉ፣ እስማኤል ሱልጣን፣ ሃይረዲን ሽፋ፣ ፈጅሩ ሱልጣን፣ ባህሩ ራህመቶ፣ ሚነወር ሀይሉ፣ ሀይልዬ ጀማልና አስማረ አለሙ የተባሉ ግለሰቦች ካልተያዙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን ድርጊቱን ፈፅመዋል ነው የተባለው።
በእግረኛ መንገድ ላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ በማከናወን ላይ የነበሩ ግለሰቦችን የደንብ ማስከበር አባላት የሆኑት ማቱሳላ ማዶሬና አቡሽ ሽጉጤ ድርጊቱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ፣ አባላቱን በድንጋይና በእርግጫ የድብደባ ወንጀል መፈጸማቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ በወቅቱ ድርጊቱን ፈጽመው ቢሰወሩም በክ/ከተማው ፖሊስ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር መቻላቸውን ፖሊስ ገልጾ፣ በፈጸሙት የወንጀል ድርጊትም ተገቢውን ምርመራ የማጣራትና ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱን መቀጠሉንም ገልጿል።
በጎዳና ላይ የሚደረጉ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች የእግረኛና የተሽከርካሪዎችን ፍሰት በማወክ ዜጎችን ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከማድረጉም ባሻገር፣ ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴን የሚጎዳ መሆኑ የሚታወቅ ብሏል ፖሊስ። ይህንንም ድርጊት ለመከላከል የተሠማሩ የጸጥታ አካላት ላይ ትንኮሳ መፈጸምና ለህግ ተገዢ አለመሆን ተጠያቂነትን የሚያስከትል ድርጊት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።












