የህንድ መንግስት ከሩሲያ በሚያስገባው የነዳጅ ምርት ዙሪያ የምዕራቡን ዓለም ጣልቃ ገብነት አወገዘ። አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት በሚያራምዱት “አታላይ አቋም” ዙሪያ ብርቱ መግለጫ አውጥታለች።
የህንድ መንግስት ከሩሲያ ነዳጅ የማስገባው ብሄራዊ ጥቅምን እና የኢነርጂ ደህንነትን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው በሚል ምላሹን ይፋ አድርጓል። ከምዕራቡ ዓለም በኩል ልክ ያልሆነ እና ምክንያት የሌለው ሀሳብ እየተጋራ ነው በሚልም መስሪያ ቤቱ ውድቅ አደርጎታል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህንድ ከሩሲያ እጅጉን የበዛ የነዳጅ ምርት በመግዛት ለጥቅም በነጻ ገበያ ውስጥ በመግባትም ትሸጠዋለች ማለታቸውን ተከትሎ ነው ኒው ደልሂ የተቆጣችው።
አሜሪካ ሳትቀር የዓለምን የነዳጅ ገበያ ለማረጋጋት ከሩሲያ የነዳጅ ምርት አገራት እንዲገዙም ታበረታታ ነበር ስትል ህንድ ምላሽ ሰታለች። በዛ ላይ ህንድን የሚያውግዙ አገራት ሁሉ ከሩሲያ ጋር የራሳቸውን ንግድ አስቀጥለዋል በሚልም ወንጅላለች።
ከሩሲያ ነዳጅ የምናስገባው የኢነርጂ ገበያውን ለማረጋጋት ነው ያለችው ህንድ፣ ከብሄራዊ ጥቅሜ አንጻር በማደርገው ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት አግባብነት የለውም በሚል ወቅሳለች።
ዘገባው የዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












