በ-ቶማይ መኮንን
August 2, 2025
የቀድሞው የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ኡርቤ የ12 ዓመት የቁም እስር እንደተፈረደባቸው ተገለጸ::

አልቫሮ ኡርቤ በሙስና ተከሰው ለስድስት ወራት ክሳቸውን ሲከታተሉ መቆየታቸውም ታውቋል፡፡ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ላይ የተለያዩ መረጃዎች ቀርበው እና ምስክሮች ለፍርድ ቤት ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ ፍርዱ ተበይኖባቸዋል፡፡
በፈረንጆቹ በ1990 ላይ የሀገሪቱን ህግና ስርዓት በተላለፈ ሁኔታ ከወታደራዊ አዛዦች ጋር በመመሳጠር ያልተገባ ጥቅም አካብተዋል በሚልም ተጨማሪ ክስ ቀርቦባቸዋል ነው የተባለው፡፡ የ73 ዓመቱ አልቫሮ ኡርቤ ፍርዱን እንደማይቀበሉ ተናግረው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ጥቃት ሲሉ ክሱን ውድቅ አድርገውታል፡፡ ዘገባው የፒቢ ኤስ ኒውስ፡፡

Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












