ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት በአካባቢ ጥበቃ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እና የተሻለ ነገን እየገነባች እንደምትገኝ ዲፕሎማቶች እና የውጭ ኢንቨስተሮች ገለጹ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሊዩ ዢያዎጉዋንግ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፋቸው ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ ለመዋጋት እና ለቀጣይ ትውልዶች የተሻለ ጊዜን ለማምጣት እያደረገ ያለው የጋራ ጥረት እንደሆነም ተናግረዋል። ቻይና ለኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና የካርቦን ልህቀት መቆጣጠሪያዎች ድጋፍ እያደረገች እንደምትገኝ አመልክተዋል።
ሌሎች ዲፕሎማቶችም አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየተወጣች ያለውን የመሪነት ሚና የሚያሳይ መሆኑን አድንቀው የተሻለ ነገን ለመስራት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑት ችግኝ መትከል ለልጅ ልጆች የሚተርፍ ትልቅ ስራ ነው፤ ወደ ኋላ መለስ ብለው በማየት ዛሬ ላይ የተከናወነውን ስራ ያደንቃሉ ሲሉ ገልጸዋል።
አረንጓዴ አሻራ እንደ ሳፋሪኮም ያሉ ኩባንያዎች ከመንግስት ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ የሚወጡት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አመልክተዋል።












