ታይላንድና ካምቦዲያ ለአምስት ቀናት የዘለቀውን የድንበር ግጭት ለማስቆም ከስምምነት ደርሰው የነበረ ቢሆንም ካምቦዲያ ስምምነቱን ጥሳለች ስትል ታይላንድን ከሳለች፡፡
በሁለቱ ሀገራት ድንበር ለአምስት ቀናት በዘለቀው ግጭት ቢያንስ 33 ሰዎች ሲሞቱ በ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡
የታይላንድ ወታደሮች እንደተናገሩት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኃላ እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ ከካምቦዲያ በኩል በበርካታ ቦታዎች የተኩስ ድምፅ መስማት መቀጠላቸውን ገልጸዋል፡፡
የካምቦዲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ለኤኤፍፒ በሰጠው መግለጫ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተደረሰ ወዲህ በሁለቱ ወገኖች መካከል “ምንም አይነት የታጠቁ ግጭቶች” እንዳልነበሩ ተናግረዋል፡፡
የተኩስ አቁም ስምምነቱ አካል የነበረው የአካባቢው አዛዦች ስብሰባ ለሁለት ጊዜ የተራዘመ ሲሆን ጨርሶ ላይካሄድም ይችላል እየተባለ ነው። በሁለቱ የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት መካከል ለዘመናት በዘለቀው የድንበር ውዝግብ ሳቢያ፣ ያለው ውጥረት ባለፈው ግንቦት አንድ የካምቦዲያ ወታደር ከተገደለ በኋላ ተባብሷል።
ባለፈው ሳምንትም አምስት የታይላንድ ወታደሮች በፈንጂ ፍንዳታ ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ ሁለቱ ወገኖች ወደ ሙሉ ግጭት ገብተዋል፡፡ይህን ተከትሎ ታይላንድ አንዳንድ የድንበር ማቋረጫዎችን ዘግታለች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የሁለቱ ሀገራት የድንበር ውዝግብ ክልላዊ መረጋጋትን ሊያናጋ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ ነው።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ – ሰላማዊት ወልደገሪማ












