ሩሲያ አንድ መቶ የሚሆኑ የዩክሬንን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አየር ላይ አከሸፍኩ አለች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ የሞስኮ ግዛቶች ላይ ጥቃቱ መሰንዘሩን አሳውቋል። በኪዬቭ እና በሞስኮ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ውይይት በቀጠለበት ሰዓት ነው ጥቃቱ የደረሰው።
እንደሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ 67 የሚሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በብሪያንስክ ፣ ስሞሊንስክ እና ካሉጋ ግዛቶች ላይ ዒላማ ሲያደርጉ ተጨማሪ 30 ድሮኖች በደቡባዊ ሩሲያ ኩርስክን ጨምሮ አየር ላይ ከሽፈዋል ።
በሞስኮ እና በሌሎች አካባቢዎችም ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖች ተመተው መውደቃቸውንም የሩሲያ መከላከያ አስታውቋል። የግዛት አስተዳዳሪዎች የተመዘገበ ጉዳት አለመኖሩን ይፋ ሲያደርጉ፣ ጥቃቱ ግን የድርድር ሂደቱን ጫና ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል በሚል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
የአገራቱን ጦርነት ለመቋጨት የምዕራቡ ዓለም የሚሄድበት ርቀት ወሳኝነት ቢኖረውም ጸብ ጫሪ ሆነዋል በሚል ክሬምሊን ይከሳል። በሌላ በኩል ሩሲያም የበዛ ፍላጎት በድርድር ሂደቶች ላይ እያሳየች መሆኑ ለሰላም ስምምነቱ እንቅፋት ሆናለች ሲሉ አውሮፓ ህብረቶችም ይወነጅላሉ።
ዘገባው የአር ቲ ነው
በ -ቢኒያም ካሴ












