“የከተማችን ቀን” በጎንደር ዩኒቨርስቲ እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት እየተከበረ ይገኛል።
ጎንደር ዩኒቨርስቲ የተመሰረተትን 70ኛ ዓመትና የማስተማሪያ ሆስፒታሉን 100ኛ ዓመት ከጥቅምት 17 ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ ይገኛል ። የእዚህ መርሃ ግብር አካል የሆነው “የከተማችን ቀን” በጎንደር ዩኒቨርስቲ እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት እየተከበረ ነው።
ጎንደር የእድሜዋንና የዝናዋን ያህል በተለያዩ ምክንያቶች በመሰረተ ልማት ሳታድግ ቆይታለች ያሉት የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን ዶ/ር) የከተማዋን የስህበት ማዕከልነት እንዲቀንስ አድርጓት ቆይቷል ብለዋል።
በአሁኑ ሰአት የከተማዋን ጥንታዊ ብሎም አንጋፋነት የሚመጥን የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው የተነሳ ሲሆን በተለይም የማህበረሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆናቸው ተጠቁሟል።
ጎንደር ዩኒቨርስቲም የከተማዋን እድገት ማፋጠን የሚችሉ ስራዎችን በከተማ አስተዳዳሩ ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱ የተነሳ ሲሆን ይህ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል። ዩኒቨርስቲው ባለፉት 70 አመታት ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጥናትና ምርምር በስፋት ሲያካሂድ ቆይቷል ተብሏል ።
በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርስቲው የ70 ኛ የምስረታ በአል እና የመማሪያ ሆስፒታሉን 100ኛ አመት ሲያከብር ዩኒቨርስቲውና የከተማ አስተዳደሩ በጋራ ለመስራት ቃልኪዳን የሚያድሱበት መሆኑን የጎንደር ከተማ ከንቲባ ቻላቸው ዳኛቸው ገልጸዋል ።
የከተማዋን እድገት ለማፋጠን ከከተማ አስተዳደሩ በተጨማሪ የአከባቢው ማህበረሰቡ ምሁራን በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባም ነው የተነሳው።
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ
( ከጎንደር)












