49 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የአውሮፕላን ፍርስራሽ በሩሲያ ምሥራቃዊ ክፍል ተገኘ።
የሩሲያ ድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ ከቻይና አዋሳኝ በሆነው የአሙር ክልል አቅራቢያ እንደተገኘ ገልጸዋል፡፡ አውሮፕላኑ 49 ሰዎችን አሳፍሮ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የተከሰከሰ ሲሆን በህይወት የተረፈ ሰውም አለመኖሩ ተዘግቦል፡፡
የነፍስ አድን ሰራተኞች የአውሮፕላኑን ፍራሽ በእሳት ነበልባል ተሸፍኖ ማግኘታቸውን የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴሩ የገለፀ ሲሆን ኤምአይ-8 ሄሊኮፕተር የአውሮፕላኑን የእሳት ቃጠሎ መመልከቱን ተናግረዋል፡፡
የግዛቱ ባለስልጣን እንደተናገሩት 43 ተሳፋሪዎች እና 6 የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ነበሩ፡፡ ይህ አውሮፕላን ደብዛው መጥፋቱ ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












