አትዮ ቴሌኮም የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን እና የሶስት ዓመት መሪ የእድገት ስትራቴጂ ማጠቃለያ ሪፖርትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ ኢትዩ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት 1መቶ 62 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል። ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ያገኘው ገቢ የእቅዱን 99 በመቶ ያሳካበት መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ያገኘው ገቢ ከ 2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ69 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። በ2016 በጀት ዓመት ኩባንያው 93 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቶ እንደነበር ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፥ የእቅዱን 73 በመቶ ያሳካበት እንደነበር ገልጸዋል።
በ- ሰላማዊት ወንድወሰን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












