የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን እና የ2017 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምን አስመልክቶ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ ከመገንባት ባለፈ፣የቁጠባ ባህል በማሳደግ የአገር ገጽታ በመገንባት የአሸናፊነት ስነልቦና የተላበስንበት ነው ሲሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ም/ዋና ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር ተናግረዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 30 2017 ዓ.ም ከህብረተሰብ ለመሰብሰብ ከታቀደው አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ የተገለጸ ሲሆን ከታቀደው የ7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄ(ዶ/ር) የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ሚዲያ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ግድቡ በሞራል፣በዲፕሎማሲ፣በገንዘብ፣ና ፐብሊክ ዲፕሎማሲን የተጠናከረበት እንደነበር የተመላከት ሲሆን ህዝቡ የሚያደርገውን ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባው ተጠቁሟል።
በሰላም ይልማ












