ከእሑድ ሌሊት ጀምሮ ሞስኮ በኪዬቭ ላይ በወሰደችው የሚሳይል ጥቃት ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ 15 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።
ጥቃቱ የተፈጸመው የዩክሬንን ጦር ለመርዳት በሚል ውይይት የፈረንሳዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂን ኖኤል ባሮት ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኪዬቭ ከደረሱ ከሰዓታት በኋላ ነው።
የዩክሬን አየር መከላከያ በበኩሉ ሩሲያ 426 የድሮን ጥቃት እና 24 የሚሳይል ጥቃት በሩሲያ እንደተፈጸመ አስታውቋል።
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪም በቴሌግራም ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ሩሲያ በኪዬቭ ላይ ሰብዓዊነት በጣሰ መልኩ ንጹሐን ላይ ጥቃት ፈጽማለች መሠረተ ልማቶቻችን ላይም ውድመት ፈጽማለች ብለዋል።
በተያያዘም ዩክሬን በሩሲያ አየር መንገድ ጥቃት ልትፈጽም ትችላለች በሚል የተነሳ በዶሞዴዶቮ እና በተለያዩ አየር መንገዶች በረራዎች መሰረዛቸው ተገልጿል።
ዘገባው የፍራንስ 24 ነው።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












