ያሳለፍነውን የውድድር አመት በውሰት ውል ጋላታሳራይ ያሳለፈው ኦሲመ ናፖሊን በመልቀቅ በቋሚነት የቱርኩን ክለብ ለመቀላቀል መስማማቱ ተዘግቧል።
ጋላታሳራይ በተጫዋቹ ዝውውር ላይ ያለፉትን ሳምንታት ከናፖሊ ጋር ውይይት ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በሁለት ምዕራፍ በጥቅል 75 ሚሊዮን ዩሮ ለመክፈል ተስማምቷል። ናይጄሪያዊው ግዙፍ አጥቂ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በ41 ጨዋታዎች ላይ ለጋላታሳራይ ተሰልፎ 37 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።
የቱርኩ ክለብ በታሪኩ በውድ ገንዘብ ያስፈረመውን ተጫዋች በተለየ የደመቀ አቀባበል ሊያደርግለት መሆኑ ተሰምቷል። የ26 አመቱ አጥቂ በነገው ዕለት ወደ ቱርክ ያቀናል የተባለ ሲሆን፣በአመት 18 ሚሊዮን ዩሮ የሚያስገኝለትን የአምስት አመት ውል ይፈርማል ተብሎም ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












