ሐምሌ 10 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀውን የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል።
ተሻሽሎ የጸደቀው አዋጁ በ26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ የተደረገበት መሆኑ መግለጫውን የሰጠቱ የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል። ማሻሻያው የተደረገውም የ6ኛው አገራዊ ምርጫ አፈጻጸም በመገምገም፣ዓለም አቀፍ ተሞክሮ በመቃኘት እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግን ታሳቢ አድርጎ መሆኑ ተጠቁሟል።
ሴቶች፣ ወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች በምርጫ ሂደቱ ይበልጥ ተሳታፊ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል። ከተሻሻሉት ውስጥ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ በተመለከተ ፓርቲው በተመሰረተበት ክልል 40 በመቶ አባላት በተጨማሪ በ6 ክልሎች በእያንዳንዳቸው 10 በመቶ አባላት እንዲኖሩት የሚደነግግ መሆኑ ተመላክቷል።
የፓርቲ እገዳ ሌላኛው ማሻሻያ የተደረገበት ሲሆን ፓርቲዎች የተቀመጠውን አሰራር ተከትለው ካልተጓዙ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ካላስተካከሉ የሚሰረዙበት አሰራርን በእግድ ለማቆየት በተሻሻለው አዋጅ ተቀምጧል።
ይህም አንድ ፓርቲ ማስተካካያዎቹን እስኪያደርግ በቀጥታ ከመሰርዝ ይልቅ እስከ 5 ዓመት ድረስ በእግድ እንዲቆይ የሚያደርግ ነው። ይህም ፓርቲው ችግሮቻቸውን አስተካክለው እንዲመለሱ የሚያስችል መሆኑን የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል።
የእጩ እና መራጮችን ምዝገባ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ይሆናል የሚሉ ሀሳቦች ቀርበውበታል።
በ-ሰላም ይልማ












