
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1924 የጀርመን መራሄ መንግስት የነበረው አዶልፍ ሂትለር በሂንድስበርግ እስር ቤት ውስጥ ሳለ ነበር ሜይን ካምፕ የተሰኘውን መጽሐፍ ሊጽፍ የቻለው፡፡
ሒትለር ሜይን ካምፕ ሲል የሰየመው መጽሐፍ ትርጉሙም የሕይወቴ ትግል የሚል ነው፡፡ መጽሐፉን የናዚ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሉም የሚጠሩት አሉ በሌላ በኩል ደግሞ ሰይጣናዊው መጽሐፍ የሚሉትም አሉ፡፡
የጀርመንን ሉዓላዊነት የሀገሩን ነገ የተሻለ ለማድረግ የተነሳሳው ሂትለር መጽሐፉን የጻፈበት ምክንያትም የሀገሩን ክብር ለማስጠበቅ በሚል ብቻ ሳይሆን መንበረ ሥልጣኑን ለመቆናጠጥ የሚያስችለውን ፖሊሲ በማሰብ ጭምር ነበር፡፡
ይህ የሂትለር ፖሊሲም የጀርመንን የበላይነት በማንጸባረቅ ማኒፌስቶ እስከመሆን የደረሰ ነው፡፡ በ19 25 እና በ1927 የታተመው መጽሐፉ ቅጽ 1 እና 2 ያሉት ሲሆን አምስት ሚሊዮን 2 መቶ ሺህ ኮፒ ታትሟል፡፡
የሂትለር የሕይወት ትግል መጽሐፍ በአስራ አንድ ቋንቋዎች ጭምር የተተረጎመ ነው፡፡ ሂትለር በሕይወት ዘመኑ ሳለም ባለ ሰባት መቶ ገጹ ይህ መጽሐፍ እስከ 9 ሚሊዮን ድረስ ተሽጧል፡፡
የሜይን ኬምፍ መጽሐፍ ጭብጥ አዶልፍ ሂትለር በፓርላመንታዊ ዴሞክራሲ እንደማያምን እና ለአምባገነንነት እና ዘረኝነት ቅድሚያ የሰጠበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
የዛሬው የዕለቱን በታሪክ ገጾችም ይህንኑ ቀን በማስታወስ የአዶልፍ ሂትለር መጽሐፍ የታተመበት ቀን ነው ሲሉ ዕለቱን አስታውሰውታል፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ












