በሊባኖስ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ በሀገሪቱ የሚገኘውን ትልቁን ግድብ ሊያደርቀው እንደሆነ ተሰማ።
በሊባኖስ ምድር አስከፊና በታሪክ አጋጥሞ የማያውቅ የተባለለት ድርቅ በሀገሪቱ የሚገኘውን ትልቁን የውሃ ግድብ በከፍተኛ ደረጃ የውሃ መጠኑን እንደቀነሰውም ተነግሯል፡፡ ከዚያ በሊባኖስ ከተከሰተው ከባድ ጋር በተያያዘም በአገሪቱ የግብርና ዘርፍ ኤሌክትሪክ ማመንጫና የመጠጥ ውሃ ላይ ከባድ የተባለ አደጋ መደቀኑ ተሰምቷል።
በሊባኖስ ታላቁ የሊታኒ ወንዝ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ፣ የወንዙ ፍሰት እና የውሃ መጠን በተለይም ወደ ካራውን ግድብ የሚገባውን መቀነሱን እና ቀድሞ 350 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዘው ግድቡ በዚህ ዓመት ግን የውሃ መጠኑ ከአርባ አምስት ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንዳላለፈ አስታውቋል።
ዘገባው የኤዢያ ዋን ነው።
በ-ትእግስቱ በቀለ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












