በ89 ዓመት ዕድሜው ማራቶን ላይ በመሳተፍ እና ውድድሩን በማጠናቀቅ ሪከርድ ያስመዘገበው ሲንግሃ፣ በፑንጃብ ከተማ በእግር በመጓዝ ላይ እንዳለ የመኪና አደጋ እንዳጋጠመው ተገልጿል።
የዕድሜ ባለጸጋውን አትሌት ወደ ሆስፒታል በፍጥነት ማድረስ ቢቻለም ህይወቱ ልትተርፍ እንዳልቻለች ተገልጿል።
ፋውጃ ሲንግሃ በዓለም ክብረ ወሰን ላይ ስሙ የሰፈረው በአውሮፓውያኑ ሚሊኒየም በለንደን ማራቶን ላይ በ89 መት ዕድሜው ተካፋይ በመሆን እና 42 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ውድድር በማጠናቀቁ ነው።
ህንዳዊው ሲንግሃ እስከ ሚሊኒየሙ የለንደኑ ማራቶን ድረስ በግብርና ሙያ ይተዳደር የነበረ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ የእንግሊዝን ዜግነት ማግኘት ችሏል። የእንግሊዝ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአዛውንቱ አትሌት ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












