በቀድሞ ስሙ ትዊተር፣ የአሁኑ ኤክስ መስራቾች የሆነው ጃክ ዶርሲ ኢንተርኔት የማያስፈልገው አዲስ የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያ ማስተዋወቁ ተዘገቧል፡፡
ቢትቻት (Bit chat) የሚል ስያሜ የተሰጠው መተግበሪያው፤ ያለ ኢንተርኔት እና ያለ ዋይፋይ መልዕክት ለመለዋወጥ የሚያችስል መሆኑ ተጠቁሟል።
ቢትቻት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ሥራ የጀመረ ሲሆን የብሉቱዝ ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ተነግሯል፡፡ መተግበሪያው ኢንተርኔት በሌለበትና በሚቋረጥበት ወቅት መልዕክቶችን ለመላላክ እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡ ቢትቻትን ለመጠቀም ኢንተርኔት፣ አካውንት፣ የስልክ ቁጥር አይፈልግም ነው የተባለው፡፡
ይህ አገልግሎት እጅግ በጣም ግላዊነትን የተላበሰ እና በብዙ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚስተዋሉ የእገዳ ስርዐትን የሚዋጋ በመሆኑ ትልቅ ቦታ እየተሰጠው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ዋትስአፕ ፣ ፌስቡክ ፣ ሜሴንጀርና X ላይ ቢትቻት አዲስ ተፎካካሪ በመሆኑ ስጋት ፈጥሯል፡፡
ዘ ኢንዲፕእንደንት እንዳስነበበው
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












