አምስተኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዘጋጅነት ሐምሌ 3 እና 4 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይካሂዳል ተባለ።
የፓርላማ ዴሞክራሲ ሥርዓት በአንድ አገር መጠናከር ለዜጎች ዴሞክራሲዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደር መስፈን፣ ለሕግ የበላይነትና ለማህበራዊ ፍትሕ መረጋገጥ ወሳኝ ነው ያለው የምክር ቤቱ መግለጫ።
በዘንድሮው ኮንፈረንስ 167 ጥናታዊ ፅሁፎች ለውድድር ቀርበው 12 የተመረጡ ሲሆን፣ የክልልና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ የአካዳሚክ፣ የጥናትና ምርምር ተቋማትና አመራሮች፣ የፓርላማ የጥናትና ምርምር ኔትዎርክ አባላትና የባለድርሻ አካላት በሚገኙበት ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
የምክር ቤቱ ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነትና ተግባራት፦ የሕዝቡን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሕጎችን ማውጣት፣ የመንግሥት የልማት እቅዶች፣ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች በአግባቡ ተፈፃሚ ሆነው የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ፣ እንዲሁም የመንግሥትና ሕዝብ ሃብትና ንብረት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል እና አስፈፃሚው የመንግሥት አካል በተጠያቂነትና በግልፅነት ስራውን እንዲያከናወን ማድረግ እንደሆነ የምክር ቤቱ መግለጫ ያመላክታል፡፡












