NBC EThiopia
July 5, 2025
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከኢፌዴሪ ባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ጋር በመተባበር ስፖርት ለአሸናፊ ሀገር በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በባሕር ዳር አለምአቀፍ ስታዲየም በመከናወን ላይ ይገኛል።

በመድረኩ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ አወያይነት አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ዶክተር አመንሲሳ ከበደ፣ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና አቶ መኪዩ መሀመድ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ ናቸው። ክብርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ፣ስፖርት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው፣የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር በመሆኑ አበክሮ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
በፓናል ውይይቱ የፌዴራል እና የክልል ስፖርት አመራሮች፣አሰልጣኞች፣የስፖርት ጋዜጠኞች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት “ስለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የውይይት እና ምክክር መድረክ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በ2 ምዕራፍ በ14 ከተሞች አካሂዷል። ይህኛው መድረክ 21ኛው ሲሆን ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
በ-አልፈሪድ ነስሮ (ከባሕር ዳር)













