ፍልስጤማዊው እግር ኳስ ተጫዋች ሙሀናድ አል-ሊሊ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት ህይወቱ ማለፉ ተዘግቧል።
ናዲ ካሃዳማት አል-ማጋዚ ለተባለው ክለብ አምበል ጭምር የነበረው ተጫዋቹ፣ ከጥቂት ቀናት በፊት የእስራኤል ሀይሎች ማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው የማግሃዚ ካምፕ ላይ በፈጸሙት የቦምብ ጥቃት ከቆሰለ በኋላ ህይወቱን ለማትረፍ የተደረገው ርብርብ ሳይሳካ ቀርቷል ተብሏል።
ሙህናድ አል-ሊሊ ጋዛ ውስጥ በእስራኤል ሀይሎች የተገደለ 439ኛው እግር ኳስ ተጫዋች እንደሆነ ዘገባው አስረድቷል። ተጫዋቹ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቅርቡ እንደፈጸመ በማህበራዊ ሚዲያ ያጋራቸው ፎቶዎች ያመላክታሉ።
የእግር ኳስ ቤተሰቡ በ20 ቁጥር ለባሹ የሊቨርፑል አጥቂ ዲዮጎ ጆታና ወንድሙ አንድሬ ሲልቫ ህልፈት እያነባ ባለበት ሁኔታ ነው ሌላ አሳዛኝ ዜና የተሰማው።
በ ይበልጣል ሰውነት
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












