Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

አጨቃጫቂው ውሳኔ አለፈ

አጨቃጫቂው ውሳኔ አለፈ

July 4, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

የአሜሪካ ኮንግረስ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትልቁ ድል ነው የተባለውን አወዛጋቢ ውሳኔ አሳለፈ።

ኮንግረሱ ያሳለፈው ውሳኔ አብዛኛውን ግብር ቅነሳ ቋሚ አድርጎ የሚያስቀጥል፣ለድንበር ደህንነት፣ለመከላከያ እና ሀይል ምርት ወጭ የሚጨምር አሊያም የሚያሳድግ ነው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 218 ለ 214 በሆነ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገር ውስጥ አጀንዳ ትልቁ የፖሊሲ ድል ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል።

ሁለት ሪፐብሊካኖች ብቻ ከዴሞክራቶቹ ጎን ቆመዋል፡፡ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት(ሴኔት) ረቂቁን በጠባብ ውጤት 51 ለ 50 በሆነ ድምጽ ማሳለፉም ይታወሳል፡፡ ይህን ትንቅንቅ የሴኔት ውጤት ለማስመዝገብ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት የጄዲ ቫንስ ገላጋይ ውሳኔን ይፈልግ ነበር፡፡

የአሜሪካ ሴኔት በምክትል ፕሬዚዳንቶች የሚመራ በመሆኑ የድምጽ ውጤቶች እኩል ሲሆኑ አሊያም ገላጋይ ሲፈልጉ ድምጻቸውን ለመስጠት ይገደዳሉ፡፡ ቫንስም ያደረጉት ይህኑ ነው፡፡ የትራምፕ ትልቁ ረቂቅ ህግ የ2017 ማለትም የቀደመ ፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የተራዘመ የግብር ቅነሳ ሀሳብ ውጤት ነው፡፡

አከራካሪው እና ግዙፉ ረቂቅ ህግ(ቢግ ቢውቲፉል ቢል) በዴሞክራሮቹ የሚሊዮን አሜሪካውያን ህይወት ላይ የተላለፈ አደገኛ ውሳኔ ነው በሚል እየተብጠለጠለ ነው። የኮንግረሱ የበጀት ቢሮ ረቂቁ 3.4 ትሪሊዮን ዶላር ለሚቀጥሉት አስርት ዓመታት በፌደራል ደረጃ ጉድለት ያመጣል ፤ሚሊዮኖችን ያለ ጤና መድህን ባዷቸውን ያስቀራቸዋል ብሏል፡፡

ዋይት ሀውስ እና ሪፐብሊካኖቹ ይህን መከራከሪያ ፈጽሞ አይቀበሉትም፡፡ ዴሞክራቷ ካማላ ሀሪስም ውሳኔውን “ሪፐብሊካኖቹ በኮንግረሱ ውስጥ ሚሊዮኖችን በመላ አገሪቱ ለማውደም ድምጽ ሰጡ ” በሚል አጣጥለውታል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም ውሳኔው ግድየለሽነት ብቻ ሳይሆን ጭካኔም ነው ብለውታል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ዴሞክራቶቹ እኔንም ፤አሜሪካንም ይጠላሉ ግን ትልቁን ድል አሜሪካ አስመዝግባለች ሲሉ በኩራት ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ በሚጓጉለት ረቂቅ ህግ ላይ ፊርማቸውን ያኖራሉ፤ፖሊሲያቸውን ለማስፈጸምም ዕድሉ እጃቸው ላይ ገብቷል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት እና ሲ ኤን ኤን እንደዘገቡት።

በ-ቢኒያም ካሴ

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EthiopiaFacebookMetatrumpUSA
ShareTweetShare
Previous Post

ፍልስጤማዊው ተጫዋች በእስራኤል ወታደሮች ተገደለ

Next Post

የቀድሞ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ፒተር ሩፋይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የቀድሞ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ፒተር ሩፋይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የቀድሞ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ፒተር ሩፋይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ለታሊባን ዕውቅና በመስጠት ፈር ቀዳጇ ሩሲያ

ለታሊባን ዕውቅና በመስጠት ፈር ቀዳጇ ሩሲያ

“በትግራይ ክልል ያለው ነባራዊ ሁኔታ የምክክር መድረክ ለማስጀመር አዳጋች ነው “ኮሚሽኑ

"በትግራይ ክልል ያለው ነባራዊ ሁኔታ የምክክር መድረክ ለማስጀመር አዳጋች ነው "ኮሚሽኑ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?