የዓለም ልዕለ ኃያሏ ሀገር አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማቋረጥ እንደሆ ተሰምቷል። ምክንያቱ ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ለራሷ ያስቀመጠችው የመጠባበቂያ ጦር መሳሪያ እጥረት እየገጠማት በመሆኑ ነው ተብሏል።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በገባችው ጦርነት ምክንያት ዋነኛ የጦር ደጋፊዋ ዋሽንግተን መሆኗ ይታወቃል። በተለይም በጆ ባይደን ዘመን በርካታ ድጋፍ እንደሚደረግላት ቃል ተገብቶላት ነበር።
በአውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር ከየካቲት 2022 ጀምሮ አሜሪካ ለዩክሬን ያደረገችው የሚሊታርሪ ድጋፍ 66 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ይነገራል። ትራም ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ደግሞ ዋሽንግተን ላወጣችው የሚሊታሪ ወጪ በምላሹ የዩክሬንን ውድ ማዕድናትን ለመውሰድ መስማማታቸ ይታወሳል።
የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ አና ኬሊ እንደተናገሩት፣ ውሳኔው የተላለፈው የአሜሪካን ጥቅም ማስቀደም ዓላማው ሲሆን፣ ሃገሪቱን በጦር መሳሪያ የማትደፈር ማድረግ የምይደራደሩበት እንደሆነ ነው የጠቀሱት። ለሌሎች ሃገራት የሚደረገው ድጋፍ ድጋሚ እንደሁኔታው የሚጠን እንደሆነ ነው ቃል አቀባይዋ የተናገሩት።
በዩኤስ ያለው የጦር መሳሪያ እጥረት መታየቱን ተከትሎ ነው ወደ ዩክሬን ሊላኩ የታሰቡት ድጋፎች ሊቋረጡ የተደረገው። ሆኖም የትኞቹ መሳሪያዎች እንዳይላኩ እንደተደርጉ ግን እስካሁን በይፋ አልተገለጸም።
ታዲያ አሁን ላይ የሩሲያ ጦር የበላይነት በያዘበት እና ክፍተኛ ጥቃት እያደረሰ በሚገኝበት ወቅት ድጋፉ መቋረጡ ዩክሬንን የበለጠ ዋጋ ሊያስከፍላት ይችላል ተብሏል።
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሰት ውሳኔውን አስመልክተው ሲናገሩ፣ አውሮፓ በመከላከሉ ረገድ ያለማንም ድጋፍ ራሷን ማጠናከር አለባት። ይሄን ሃሳብ ትራምፕ በማቅረባቸውም እውቅና ሊሰጣቸ ይገባል ሲሉም ተሰምቷል።












