June 30, 2025
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዓለምአቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ተቀብለው አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስመልክቶ በማህበራዊ የትሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ፦

“ዛሬ ጠዋት በሬይስ ኦፍ ሆፕ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከመጡት የአለምአቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ(IAEA) ዋና ዳይሬክተር ማሪያኖ ግሮሲ ጋር ተገናኝተናል። የአለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ በካንሰር ሕክምና ክብካቤ፣ የእንስሳት ጤና፣ የፀፀ ፍላይ ዝንብ ማጥፊያ፣ በኒኩለር ኢንጂነሪንግ እና የቁጥጥር ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ ነው። ውይይታችን በመካሄድ ላይ ባሉ ድጋፎች እና የወደፊት የትብብር እድሎች ላይ ያተኮረ ነበር።” ብለዋል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












