June 30, 2025
ዶናልድ ትራምፕ ሀብታም የአሜሪካ ኢንቨስተሮች ቲክቶክን ለመግዛት ዝግጁ መሆናቸውን አሳወቁ፡፡ ቲክቶክን ለመግዛት ግን የቻይናን ፈቃድ ማግኘት ቅድሚያ ይፈልጋል ብለዋል ሪፐብሊካኑ ትራምፕ።

የገዥዎቹን ስም ዝርዝር በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ አደርጋለሁ ያሉት ትራምፕ፣ የቤይጂንግን ፈቃድ መጠበቅ ግን ያስገድዳል ብለዋል፡፡ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በቀላሉ የባይትዳንስን ሀብት አሳልፈው እንደማይሰጡም እየተነገረ ነው፡፡
“ቲክቶክን የሚገዛ ሰው አለ፤ እንደማስበው ግን የቻይናን ፈቃድ ይጠይቃል፤ ፕሬዚዳንት ሺም ይህን ሊያደርጉት ይችላሉ” በሚል ሀሳባችውን አጋርተዋል ትራምፕ፡፡
የሀብታሞች ስብስብ ገዥ እንዳለን ግን ይታወቅልን ሲሉ በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ ቻይናን እና አሜሪካን ከማያግባቧቸው ጉዳዮች መካከል የቴክኖሎጂ ውድድር አንዱ እየሆነ መጥቷል፡ዘገባው የፎክስ ኒውስ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












