የሩሲያ ዩክሬን ሶስተኛው ዙር ድርድር ከእስረኞች ልውውጥ በኋላ በኢስታንቡል የሚካሄድበት ቀን ይቆረጥለታል ተባለ።
የክሪሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ እስረኞችን ከተለዋወጥን በኋላ ሶስተኛውን ዙር ድርድር የምናረግበትን ዕለት እንወስናለን ብለዋል። ሩሲያና ዩክሬን ባለፈው የፈረንጆቹ ሰኔ 2 በኢስታንቡል ባካሄዱት ሁለተኛው ዙር ቀጥተኛ ድርድር የሰብአዊ ስምምነት ለመስራት ለማከናወን ተስማምተዋል።
እስረኞችን መለዋወጥና ሌሎችም ስምምነቶች ተፈፃሚነት ካገኙ በኋላ የሶስተኛው ዙር ድርድር ቀን መቁረጥ ያስችላል ብለዋል ፔስኮቭ። ሩሲያና ዩክሬን አንድ ሺ ታሳሪዎች በአንድ ሺ ለመለዋወጥ እንዲሁም ታማሚና ከ25 ዓመት በታች የሆኑ አገልጋዮችን ለመለዋወጥ መስማማታቸው ይታወሳል።
ዘገባው የአናዶሉ ነው
በ-ቶማይ መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












