የውይይት መደረኩ ሴንተር ፎር ሪስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉል ፖለቲክስ (Center for responsible and peaceful politics) ከኢዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
በመርሃግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ሰላም፣ልማትና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ወጣቱ ከመከረ ብዙ እናተርፋለ፤ ጎደለን ብለን በሚያጎል መንገድ ከመጓዝ ይልቅ የጎደሉ ሀሳቦች ላይ መምከር ይገባል ብለዋል።
እስካሁን በርካታ የግጭት ሂደቶች መታለፋቸውን ያነሱት የሰላም ሚኒስትሩ እስከዛሬ ያለፍንባቸውን መንገዶች በመተው ሰላማዊ መንገድ መምረጥ ድፍረት ይፈልጋል ነው ያሉት።
የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ”ግጭት አጣው ያልከውን ይበልጥ ያሳጣሀል እንጂ ትርፍ አያስገኝም” በማለት ወጣቱ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት ማድረጉ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል። በትግራይ ጉዳይ ላይ እየመከረ የሚገኘው መድረክ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በጥቂት ሰነፎች ምክንያት የትግራይ ህዝብ ወደ ማይፈልጉት ማጥ መግባቱ ሊቆም ይገባል ብለዋል። የትግራይ ህልውናን ለማረጋገጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል።
የውይይት መደረኩ ሴንተር ፎር ሪስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉል ፖለቲክስ (Center for responsible and peaceful politics) ከኢዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ሰላም፣ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎች እና ፈተናዎች በሚል ሀሳብ ላይ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
ሰላማዊና ዲሞክራሲ የሰፈነበት የትግራይ ክልልን ለመገንባት አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ትኩረቱን ባደረገው የውይይት መድረክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የትግራይ ተወላጆች ታድመውበታል።
በ ሰላም ይልማ












