የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ የሙስና ክስ እንዲነሳ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ኔታንያሁ በፈረንጆቹ 2019 በሙስና እና እምነት በማጉደል ወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው እና እስካሁን መቀጠሉን ተከትሎ ነው ትራምፕ ክሱ እንዲነሳ ጥያቄ ያቀረቡት የተባለው፡፡
በፈረንጆቹ 2022 በፍርድ ቤት ክርክር ላይ የሚገኙት ኔታንያሁ፣ በተመሰረተባቸው ክስ ላይ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተከራክረዋል፡፡ “ለእስራኤል መንግስት ባለውለታ ለሆነው ታላቁ ጀግና ቢቢ ላይ ለተመሰረተው የሙስና ክስ ምህረት ሊደረግበት ይገባልም” ብለዋል ትራምፕ፡፡
ኔታንያሁ ነገሮችን በጥልቀት የሚመረመርበት (WITCH HUNT) ስልቱ በጣም ይመሰጥኛል ሲሉም ትራምፕ አሞካሽተዋቸዋል፡፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ባለፈው ሰኔ 3 በቴላቪቭ የኔታንያሁ ጉዳይ እንደገና መነሳቱን ተከትሎ ነው ትራምፕ ከኔታንያሁ ጎን መሆናቸውን ያሳዩት የተባለው ።
አልጀዚራ እንደዘገበው
ቶማይ መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












