። ። ። ። ። ። ። ። ።
የግብጽ ባለስልጣናት እና የመብት ተሟጋቾች፣ በሲና በረሃ በኩል የሃምሳ ኪሎሜትር ጉዞን በማድረግ ወደ ጋዛ ለማቅናት ያቀዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መባረራቸውን ገልጸዋል።
ይሁንና የጉዞ አዘጋጆች ጉዞውን የመሰረዝ እቅድ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የመብት ተሟጋቾች እና አክቲቪስቶች “ዓለማቀፋዊ ጉዞ ወደ ጋዛ” በሚል መሪ ቃል በጋዛ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቃወም ያለመ ጉዞ ነገ ለማድረግ ውጥን መያዛቸው ይታወቃል።
ከ80 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎች በሚሳተፋበት ጉዞ ቢያንስ 4ሺ በላይ ሰዎች ይሳተፋበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
ጉዞው በጋዛ እየደረሰ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ዓለማቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ፣ በራፋህ ያለውን መተላለፊያን ለመክፈት እና ዕርዳታ እንዳይገባ የተጣሉ ክልከላዎች እንዲነሱ ጫና ለመፍጠር ያለመ ነው ሲል የዘገበዉ ዋሽንግተን ፓስት ነው።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን












