። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
የእስራኤል መከላከያ በኢራን የኑክሌር እና ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ከባድ የአየር ጥቃት ማድረሱን አሳወቀ፡፡
ኢራንም የእራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር ክልሏን ሙሉ በሙሉ መዝጋቷን አስታውቃለች፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እንደአስፈላጊነቱ ጥቃቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
አያቶላህ አሊ ኻሚኒም እስራኤል ከባዱን ዋጋ ትከፍላለች ሲሉ ዝተዋል።
እስራኤል በስድስት የኢራን አካባቢዎች ላይ የተቀናጀ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን፣ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን አንቀሳቅሳለች ተብሏል።
ከኢራን በኩል ከባድ አጸፋ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ እንደሚፈጸምም እየተነገረ ነው።
የመጀመሪያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የእስራኤል ጦር በስድስት ስፍራዎች ላይ በመላ ኢራን ጥቃት ሰንዝሯል።
ሁለት ዙር የጥቃት ማዕበል በኢራን ላይ መድረሱን የቴህራን ሚዲያዎች ያረጋገጡ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ሶስተኛው ዙር ጥቃት ሊፈጸም ጫፍ ላይ ደርሷልም ተብሏል፡፡
ቴህራን፣ ናታንዝ፣ ታብሪዝ፣ ኢስፋሃን፣ እና መሰል ቦታዎች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ እና ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል፡ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












