
የህንዱ አየር መንገድ ቦይንግ 787-8 የመንገደኞች አውሮፕላን 242 ሰዎችን አሳፍሮ ከህንድ አህመድባድ ወደ ለንደን በመጓዝ ላይ ሳለ አየር ላይ ብዙም ሳይቆይ አደጋው ገጥሞታል።
በአውሮላኑ 169 የህንድ ፡ 53 የብሪታንያ እና አንድ ካናዳዊ እና ሰባት የፖርቹጋል ዜጎች እንደነበሩ የህንድ አየር መንገድ አስታውሷል።
የአውሮፕላኖችን በረራ እና ካርታ በግክጽ ለይቶ በማስቀመጥ የሚታወቀው የስዊድኑ ፍላይትራዳር 24 ፡የአውሮፕላኑን የመጨረሻ ምልክት ያገኘው በ625 ጫማ (190ሜ) ከፍታ ላይ ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ነው ብሏል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት አውሮኘላኑ ስለገጠመው ችግር እንዲሁም ጉዳት የተባለ ነገር የለም።
በሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












