Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

“የሰላምን ፋይዳ የምናውቀው በንድፈ ሃሳብ ሳይሆን አጥተናት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

June 11, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ሦስተኛው የሃይማኖት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ “ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበር እና ለአብሮነት” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ኮንፈረንሱ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።በኮንፈረንሱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሰላም ኮንፈረንስ በአማራ ክልል መካሄዱ ለአማራ ክልል ሕዝብ ትርጉሙ ትልቅ ነው ብለዋል። ኮንፈረንሱ ስለ ሰላም፣ ስለ አብሮነት የሚመከርበት እና ሰላም ሥር እንዲሰድ የሚያደርግ መኾኑን ገልጸዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ዋና ዓላማቸው የሰው ልጅ እና ፈጣሪን ማገናኘት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በዓለማዊ ሕይዎቱም የተቃና እንዲኾንም አስተዋጽኦ አላቸው ነው ያሉት።

የሰው ልጅ ሁልጊዜ መቻቻልን እና ሰላምን ላይፈጥር ይችላል፣ በመቻቻል እና በሰላም እንዲኖር የሚያደርጉት በውስጣችን ያሉት እሴቶች ናቸው ብለዋል። እሴቶች የሚገኙት ደግሞ በሃይማኖት ተቋማት ነው፣ የሃይማኖት ተቋማት በሕዝብ መካከል ትስስር እንዲኖር፣ የሕዝብ እና የመንግሥት ግንኙነት ጤናማ እንዲኾን ያደርጋሉ ነው ያሉት።

አሁን ላይ የሰው እና የተፈጥሮ ግንኙነት ተዛብቷል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ሰው እና ተፈጥሮ ተስማምቶ የሚገናኝባቸው የሃይማኖት ተቋማት መኾናቸውንም ገልጸዋል።

የጋራ አንድነት እንዲጸና፣ የሀገር ሰላም እንዲረጋገጥ ኮንፈረንሱ ትልቅ አቅም እንዳለው ተናግረዋል። ከንግግር ባለፈ በተግባር እና በአኗኗር ሰላማዊ መኾን እንደሚገባም ገልጸዋል። በኮንፈረንሱ የሚነሱ ጉዳዮች ውጭ ላይ ወጥተው በኅብረተሰቡ ዘንድ ጠቃሚ እንዲኾኑ እንፈልጋለን ነው ያሉት።

ኮንፈረንሱ ፍሬያማ የሚኾነው በአዳራሽ የተወሰነው ውሳኔ፣ የተመከረው ምክር በሕዝቡ ዘንድ ደርሶ በተግባር ሲኖር ነው ብለዋል።

በኩራት የምንናገራቸው በጎ ታሪክ አሉን ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ከበጎ ታሪኮች በተጓዳኝ መታረም ያለበት የግጭት አዙሪትም የታሪካችን አንድ አካል ነው ብለዋል። ግጭቱ ደግሞ ድህነትን እየመገበ ሀገርን መጉዳቱን ተናግረዋል።

ግጭትን ማቆም እንችላለን ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ችግሮችን በውይይት እና በምክክር መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል። ከትልቅነት ያወረዱንን ግጭት እና ደህንትን መታገል እና ማረም ይገባናል ነው ያሉት። የሃይማኖት ተቋማት ደግሞ ይሄን ለማረም ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል።

ሃይማኖቶች የውስጥ ችግራቸውን መፍታት፣ እርስ በእርስ ያላቸውን ግንኙነት ማስተካከል እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ሚዛኑን የጠበቀ የመንግሥት እና የሕዝብ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል። የጋራ የኾነውን ሕዝብ ለመጥቀም መሥራት ይገባል ነው ያሉት። ሰላምን ለማጽናት መንግሥት እና የሃይማኖት ተቋማት በጋራ መሥራት ይገባቸዋል ብለዋል።

የቋንቋ፣ የሃይማኖት እና ሌሎች ልዩነቶችን የአብሮነት ምንጭ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል። የሃይማኖት ተቋማት ሰላምን ከማጽናት እና አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ለሀገር ዕድገት እና ለልማት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አመላክተዋል።

መልካም አሥተዳደር እንዲሰፍን እና ግብረ ገብነት እንዲሰፍን ማድረግ ይገባቸዋል ነው ያሉት። የሰውን ሃብት የሚጸየፍ፣ አምላኩን የሚፈራ፣ ሰውን የሚያከብር ትውልድ እንዲፈጠር መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።የተዛቡ ግንኙነቶችን ማደስ እና በአንድነት መሥራት እንደሚጠበቅም አንስተዋል።

“የአማራ ክልል መሪዎች እና ሕዝብ የሰላምን ፋይዳ የምናውቀው በንድፈ ሃሳብ ሳይኾን አጥተናት ነው” ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የሰላም ኮንፈረንሱን በአማራ ክልል ማዘጋጀት ልዩ ትርጉም ስለነበረው በደስታ ተቀብለን በአጭር ጊዜ አዘጋጅተናል ነው ያሉት። ኮንፈረንሱ የሰመረ እንዲኾን ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ለሀገራችን አንድነት እና ለሕዝባችን አብሮነት ይህን አደረግን የምንልበት ጉባኤ እንዲሆን እመኛለሁም ብለዋል። ዘገባው የአሚኮ ነው፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

ጀርመናዊው ሊሮይ ሳኔ ወደ ቱርኩ ጋላታሳራይ በነጻ ለመጓዝ ተስማማ።

Next Post

የአትሌት ገለቴ ቡርቃ ባለቤት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የአትሌት ገለቴ ቡርቃ ባለቤት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የአትሌት ገለቴ ቡርቃ ባለቤት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ለ29 ጊዜያት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ለእስር የተዳረገው ማርቲን ሉተር ኪንግ

ለ29 ጊዜያት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ለእስር የተዳረገው ማርቲን ሉተር ኪንግ

የሰኔ 04/2017 ዓ.ም የቀን ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት | Live | Ethiopia

የሰኔ 04/2017 ዓ.ም የቀን ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት | Live | Ethiopia

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?