NBC Ethiopia
በ – ዳዊት ዓለሙ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፣ ሩሲያ ሌሊቱን በሰባት ሚሳኤሎችና በ315 ድሮኖች ከባድ ጥቃት ማድረሷን አስታወቁ።
አሜሪካ አስገዳጅ ጫና በመፍጠር ሩሲያን ወደ ሰላም ንግግሩ እንድትመጣ ማድረግ አለባት ብለዋል ዘለንስኪ።
ጥቃቱ ዒላማ ያደረገው ዋና ከተማዋን ኪዬቭን እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ሁሉንም ሚሳኤሎችና 228ቱን ድሮኖች አክሽፈናቸዋል ብለዋል።
በሌላ በኩል የኦዴሳ ከንቲባ ጄነዲ ትሩክሀኖቭ፣ በከተማቸው ላይ በደረሰ ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል ነው ያሉት።
የሩሲያ ባለስልጣናት በበኩላቸው፣ ዩክሬን የድሮን ጥቃት የፈጸመች ቢሆንም የደረሰ ጉዳት ግን የለም ብለዋል። ይሁን እንጂ የሞስኮ እና የሴንት ፒተርስበርግ የአየር መንገዶች በጊዜያዊነት ስራ ማቆማቸውን ግን አልሸሸጉም። ዘገባው የአልጀዚራ ነው
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia