ኢትዮጵያ መድን የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
ረፋድ 3፡30 ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እየተፋለመ የሚገኘው መቐለ ሰባ እንደርታ ከኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ መድን ሻምፒዮንነቱን አረጋግጧል።
ዋሳዋ ጆኦፍሪ የቡናማዎቹን ግብ አስቀድሞ ሲያስቆጥር ሙሉጌታ ወልደ ጊዮርጊስ አቻ ማድረግ ችሏል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን ነገ ከመቻል ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ 2 ጨዋታዎች እየቀሩት የሊግ ዋንጫ አሸነፊ ሆኗል።
የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ቡድን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ባለድል መሆን ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












